Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያየ ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን አስታወቀ።

ተሽከርካሪዎቹ ሕይወት አድን ድጋፍን ጨምሮ መድኃኒቶችን፣ የወደሙና የተጎዱ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚያገልግል እንዲሁም የተጎዱ ሰዎችን ለማከም የሚረዳ ቁሳቁስ የጫኑ ናቸው።

ተጨማሪ ድጋፎች በጉዞ ላይ መሆናቸውን ከድርጅቱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ቀደም ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በጎንደር በኩል ሽረ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ትግራይ ክልል መግባቱን ዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታውቋል፡፡

ይህ የነፍስ አድን ድጋፍ ለሴቶች እና ህጻናት ወሳኝ መሆኑን ነው ድርጅቱ የገለፀው፡፡

በቀጣይም አፋር እና አማራ ክልልን ጨምሮ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ተጨማሪ ድጋፎች እንደሚደርሱ ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኩል የሰብዓዊ ድጋፍ እና የሕክምና ቁሳቁስ የጫኑ ሥድስት ተሽከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version