Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የምርምር ስራ ለሰሩ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎችና አሳታሚዎች እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በየኮሌጆቹ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተመራማሪዎች፣ ተማሪዎችና አሳታሚዎች እውቅና ሰጥቷል።

በስድስት ኪሎ ግቢ በተዘጋጀው መርሃ-ግብር ከዩኒቨርሲቲው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሰጣቸው ተመራማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱ የተሰጣቸው ምሁራን የምርምር ስራዎቻቸው አግባብ ባላቸው ጆርናሎች ያሳተሙ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ እና በማህበረሰብ ግልጋሎት የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ መሆናቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ ከ 2 ሺህ 800 በላይ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ የምርምር ስራዎች ለህትመት እንዳበቃ በመርሀ-ግብሩ ላይ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ባለፉት ስድስት ወራት 14 የምርምር ጽሁፎችን በማሳተም እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version