Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከውጭ ለሚገቡ እንግዶች መቆያ ተጨማሪ 10 ሆቴሎች ተዘጋጁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከውጭ ለሚገቡ እንግዶች ለ14 ቀን መቆያ እንዲያገለግሉ ከተመረጡ ሁለት ሆቴሎች ተጨማሪ 10 ሆቴሎች መመረጣቸውን ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከሚገኙ ከደረጃ አንድ እስከ 5 የተካተቱ 130 ሆቴሎች ውስጥ ተጨማሪ ለመምረጥ ልየታ እየተሰራ ነው ተብሏል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ቦርድ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር እንደገለጹት፥ ህብረተሰቡ የተለመደውን አክብሮት እና እንግዳ ተቀባይነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሮና ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እና ሁሉንም የሚይዝ ቫይረስ እንደመሆኑ መጠን የውጭ ሃገር ዜጎች ላይ ማነጣጠር እንደማይገባም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ቢኒያም አስራት በበኩላቸው ቫይረሱን ለመግታት ለሚደረገው ጥረት ሆቴሎች የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ብለዋል።

ሆቴሎቹ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እንግዶቻቸውን ለማስተናገድ መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።

 

በፀጋዬ ንጉስ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Exit mobile version