አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጋና የውጭ ጉዳይ ቢሮ የመጡ የቴክኒክ ኮሚቴ ልዑካን በሳይንስ ሙዚየም ተገኝተው ለዕይታ ክፍት የሆኑ ምርትና አገልግሎቶችን ጎበኙ፡፡
ጎብኚዎቹ በሰጡት አስተያየት በኢመደአ በሚገኘው ኢትዮ-ሰርት ዲቪዥን በሀገሪቱ ላይ የሳይበር ጥቃት እንዳይከሰት 24/7 የሚያደርገውን የሳይበር ጥቃት ክትትልና ቁጥጥር አድንቀዋል።
አያይዘውም ከተቋሙ ጋር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለጻቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መረጃ ያመላክታል፡፡
በአስተዳደሩ ውስጥ በኢትዮ ሳይበር ታለንት ማዕከል ለታዳጊዎች እያደረገ የሚገኘውን ድጋፍ እና የሰሩትን የቴክኖሎጂ ውጤት አንድ ትልቅ ጅምር ነው ብለዋል፡፡

