Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

17ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በድሬዳዋ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኅብረብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ሐሳብ 17ተኛው የብሐር፣ ብሔረሰቦና ሕዝቦች ቀን በድሬዳዋ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

በአከባበሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ዛሃራ ዑሙድ÷ በዓሉን ስናከብር የአንድነት መንፈስን የሚያሰርፁ ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፈቲያ አደን÷ ድሬዳዋ የተለያዩ ብሔሮች ብሔረሰቦችንና ሕዝቦችን አቅፋ የምትኖር የትንሿ ኢትዮጵያ ተምሳሌት መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ይህን ዕሴት ለማስቀጠልም ወንድማማችነትና አብሮነትን የሚያጎለብቱ ሥራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

በቲያ ኑሬ

Exit mobile version