አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሰላ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት የትራንስፖርት አገልግሎት እንደቆም ውሳኔ ተላለፈ።
በዚህ በከተማዋ ባጃጆች እና ታክሲዎች አገልግሎት እንደይሰጡ መታገዳቸውን ከከተማዋ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በእገዳው መሰረትም ከገጠር ወደ ከተማ እና ከከተማዋ ወደ ገጠር በታክሲዎች ሲሰጥ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት መታገዱም ነው የተነገረው።
ህብረተሰቡም ራሱን ከኮሮና ቫይረስ ራሱን ለመከላከል መንግስት የሚያሳልፋቸውን ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲያደርግ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።

