Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፖሊስ ሰራዊት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ እድገት ማሳየቱ ተስፋ ሰጪ ነው -አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጭር ጊዜ ውስጥ የፖሊስ ሠራዊት ከፍተኛ አድገት ማሳየቱ ተስፋ ሰጪ ሆኖ አግኝተነዋል ሲሉ በተባበሩት ዐረብ ኢሚሬቶች የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ገለጹ፡፡

በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች የፌደራል ፖሊስ የሪፎርም ሥራዎችን መጎብኘታቸውን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደሮቹን ወክለው ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ የፖሊስ ሠራዊት እድገት እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ተስፋ ሰጪ ሆኖ አግኝተነዋል ሲሉም ነው የገለጹት።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የፖሊስ አዛዦች ህብረት ድርጅት ሊቀመንበር ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው ÷ የለውጡ መንግስት ለሪፎርሙ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠቱ በተከናወነው ተጨባጭ የለውጥ ተግባራት አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኢትዮጵያን በሚመጥን ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡

Exit mobile version