Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሦሥት ዘርፎች የተሠማሩ ደላሎች ፈቃድ እንዲሰረዝ አድርጌያለሁ – የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦሥት ዘርፎች የተሠማሩ ደላሎች ፈቃድ እንዲሰረዝ ማድረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በእህል ፣ በቁም እንስሳት እና በአትክልት እና ፍራፍሬ የተሰማሩ የ8 ሺህ 517 ደላሎችን ፈቃድ ነው ሚኒስቴሩ እንዲሰረዝ ያደረገው፡፡

በሚኒስቴሩ የፈቃድ እና ቁጥጥር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጅራታ ነመራ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት ÷ ደላሎቹ የገበያውን ዋጋ ከማናር በዘለለ ምንም የሚጨምሩት ዕሴት የለም።

በመሆኑም ሚናቸውን በማጤን ፈቃዳቸው እንዲሠረዝ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ደላሎቹ በሌሎች ቋሚና ተንቀሳቃሽ ዘርፎች ብቻ ተወስነው የማገናኘት ሥራ እንዲሰሩ እና በእነዚህ ሦስት ዘርፎች ላይ ግን ያላቸው ሚና በኅግ እንዲመክን መደረጉን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ግብይቶች በደረሰኝ እንዲካሄዱ በማድረግ ደላላውን የመቆጣጠር ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

Exit mobile version