Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአዲስ አበባ ፖሊስ ተጨማሪ አዲስ የደንብ ልብስ ሥራ ላይ አዋለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ተጨማሪ አዲስ የደንብ ልብስ ሥራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የፖሊስ ተቋማትን ለማዘመን በተያዘው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ መሰረት የአዲስ አበባ ፖሊስ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን አስመርቆ እየተገለገለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ከዚህ ቀደም ለተወርዋሪ ኃይል ሲጠቀምበት ከነበረው የደንብ ልብስ በተጨማሪ ከነገ ጀምሮ ተጨማሪ የደንብ ልብስ ሥራ ላይ እንደሚውል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ይህንን የደንብ ልብስ የለበሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት መሆናቸውን ተገንዝበው ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ መገልገልም ሆነ አስመስሎ መጠቀም የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ የጸጥታ አካላትን የደንብ ልብስ የሚገለገሉም ሆነ አመሳስለው የሚጠቀሙ አካላት ከሕገወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version