Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር በምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴንማርክ የልማት ትብብር ሚኒስትር ዳን ጀርገንስ በአዲስ አበባ ከተማ በምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የተሰሩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
 
በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይን ጨምሮ የዓለም ባንክ ካንትሪ ዳይሬክተር ፣ የፌዴራል፣ የዓለም ባንክና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
Exit mobile version