አዲስ አበባ ፣ ጥር 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች ልዑክ በምስራቅ ጎጃም ዞን ሉማሜ ከተማ አስተዳደር የሚገኘውን አባይ የቆርቆርና ሚስማር ፋብሪካ ጎበኘ።
አመራሮቹ “ኢትዮጵያ ታምርት በሚል”በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር በተዘጋጀ የአምራች ኢንዱስትሪዎችና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የውይይት ፎረም ላይ እንደሚታደሙ የምስራቅ ጎጃም ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

