Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በወላይታ ዞን ከ102 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የበዴሳ ኮንስትራክሽንና ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ከ102 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የበዴሳ ኮንስትራክሽንና ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ ተመርቋል፡፡

የኮሌጁ የግንባታ ስራ በ2008 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን ፥ በተለያዩ ምክንያቶች ቢጓተትም ቅድሚያ ተሰጥቶ ግንባታው እንዲጠናቀቅ መደረጉን የደቡብ ክልል ቴክኒኪና ሙያ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር እንዳልካቸው ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ባሉ ስራዎችም የዞኑና የወረዳው አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ከተማና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ፣ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር እንዳልካቸው ጌታቸው፣ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች የኮሌጁን የአውደ ጥናት ሥፍራዎችን፣ ቢሮዎችን እና መማሪያ ክፍሎችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።

በማህሌት ኡኩሞ

Exit mobile version