Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሀገራዊና ከተማዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገራዊና ከተማዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ፡፡

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል፡፡

መድረኩ አዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ ወዲህ ባሳካቻቸው ስራዎች፣ ፋይዳዎቻቸውና ተግዳሮቶች እንዲሁም መፍትሔዎችን መሰረት አድርጎ አሁን የሚገጥሙ ፈተናዎችን እንዴት መሻገር እንደሚገባ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

በመድረኩ አቶ አዳም ፋራህ እንደገለጹት÷ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ በከተማው የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ስራዎች መስራትና የኢኮኖሚ ተዋንያኑ ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ማድረግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡

ጽንፈኝነት በሀይማኖትም ይሁን በብሔር መልክ የሚገለጽ መሆኑን ጠቅሰው÷ጥርጣሬንና አለመግባባትን የሚያነግስና ለብልጽግና ጠንቅ በመሆኑ አስተሳሰቡንና ድርጊቱንም መታገል ይገባል ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በበኩላቸው÷ አዲስ አበባ ከተማ በርካታ ታላቅ ፕሮጀክቶችን በመገንባት የከተማዋን ገጽታ መቀየር ከመቻሏም በላይ በሰው ተኮር የልማት ስራዎች የህዝቡን ችግር ማቅለል ያስቻሉ ውጤቶች መመዝገባቸውን  ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የተጀመረው የጸረ ሌብነት ትግል፣አገልግሎቶችን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

በነጻ ሚዲያ ስም በሕዝቦች መካከል አለመተማመንን ለማንገስ ሀሰተኛ ወሬዎችን በሚዲያ በሚያናፍሱት ላይም ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው÷ ከተማዋ ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች አመራሩ በእምነትና በዕውቀት ስራውን መምራት በመቻሉ መሆኑን ጠቅሰው ከስኬቶች በመማር ለቀጣይ የላቀ ስራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version