Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ክልል በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ሰብዓዊ መብቶች እንዳይጣሱ ኢሰመኮ ባለሙያዎቹን አሰማራ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በደቡብ ክልል በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ሰብዓዊ መብቶች እንዳይጣሱ ለመከታተል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎቹን ማሰማራቱን አስታወቀ፡፡

የባለሙያዎቹ ቡድን በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በሚገኙ ሥድስት ዞኖች ማለትም ጋሞ፣ ወላይታ፣ ጎፋ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ÷ እንዲሁም አምሥት ልዩ ወረዳዎች ማለትም ቡርጂ፣ አማሮ፣ ባስኬቶ፣ ዲራሼ እና አሌ በሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ የሰብአዊ መብቶችን ሁኔታ ይከታተላል ተብሏል፡፡

ግለሰቦችና መንግስታዊ ተቋማት ኮሚሽኑ ላሰማራቸው የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ቡድን አባላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሲያጋጥም በ7307 ነጻ የሥልክ መስመር መጠቆም እንደሚገባ አመላክቷል፡፡

ኮሚሽኑ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለመተባበር እና ኃላፊነቱን ለመወጣት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version