Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጅማ ዩኒቨርሲቲ 200 አልጋዎቹ ያለት የኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል አዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል 200 አልጋዎቹ ያለት የኮቪድ-19/ኮሮና ቫይረስ/ የህክምና ማዕከል ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ማዕከሉ በቫይረሱ የተጠረጠሩ 3 ሺ ሰዎች የሚስተናገዱበት የለይቶ ማቆያ ስፍራ እንዳለውም ተገልጿል።

300 የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና መውሰዳቸውን ያስታወቁት በዩኒቨርስቲው የህክምና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሀመድ አባ መጫ ለማዕከሉ የሚያስፈልጉ የላብራቶሪ፣ መካኒካል ቬንትሌተርና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶች መሟላታቸውን ጠቁመዋል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባ ፊጣ በበኩላቸው ሳኒታይዘርና ቫይረሱን ለመከላከል የሚያግዙ ሌሎች ግብአቶችን ለማዘጋጀት ችግር ፈቺ ምርምሮች እየተደረጉ ነው ብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ከባለሀብቶችና ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ተጋላጭ የሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከቤተሰቦቻቸው የማገናኘት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግራል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል የተዘጋጀው የኮቪድ 19 ማከምያ ማዕከል በዚህ በሳምንት መጨረሻ ላይ አገልግሎት እንደሚጀምር ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
በሙክታር ጠሃ

Exit mobile version