አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ ግጭት ምክንያት የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ወደ ሥራ የመመለሱ ተግባር 95 በመቶ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ለ59 ከተሞች /ዞኖች/ ወረዳዎች አገልግሎቱን ዳግም ለመመለስ ታቅዶ እስከ አሁን ለ56 አገልግሎቱን ዳግም ማቅረብ መቻሉ ተገልጿል፡፡
በዚህም በሰሜኑ ግጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ወደ ሥራ የመመለሱ ተግባር 95 በመቶ መጠናቀቁን ነው ተቋሙ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጸው፡፡
በአፋር ክልል ኤርቤቲ ከተማ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ለጊዜው አገልግሎቱን በጄኔሬተር ለማቅረብ እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡
እስከ አሁን በሦስቱም ክልሎች የወደመውን መሠረተ ልማት በጊዜያዊነት መልሶ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ በተደረገው ጥረት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡
በሌላ በኩል ከወልዲያ 33 ኪሎ ቮልት ኃይል የሚያገኙትን ሦስት የአፋር ከተሞች/ወረዳዎች (ጭፍራ፣ ሱኑታ፣ አውራ) ወደ አገልግሎት ለመመለስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል መጠናቀቅ የሚገባቸው ሥራዎች እየተጠበቁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
አካባቢዎቹ ኃይል እንዲያገኙ በሚያደርገው መስመር ላይ የሚከናወነውን የመቆጣጠሪያ ሥራ በአንድ ሣምንት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መናገራቸው ይታወሳል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!