አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባ ለኮቪድ -19 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አጸደቀ።
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትና የጉዳትን መጠን ተከታትሎ በየጊዜው ለምክር ቤቱ ሪፖርት የሚያቀርብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላትን የሰየመው ከምክርቤቱ አባላት መካከል ነው።
በዚህ መሰረት፡-
1ኛ – አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት — የቦርዱ ሰብሳቢ
2ኛ – አቶ ተስፋዬ ዳባ ————የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ
3ኛ- ወይዘሮ ፋንታዬ ወንድም —–የቦርድ አባል
4ኛ- አቶ ሽኩሪ መሀዲን———–የቦርዱ አባል
5ኛ- ዶክተር ብሩክ ላጲሶ ———-የቦርድ አባል
6ኛ- ወይዘሮ ሞሚና መሀመድ—— የቦርድ አባል
7ኛ – አቶ በሻላ ገመቹ ————- መርማሪ ቦርድ አባላት ሆነው ተሰይመዋል።
1ኛ – አቶ ጴጥሮስ ወልደሰንበት — የቦርዱ ሰብሳቢ
2ኛ – አቶ ተስፋዬ ዳባ ————የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ
3ኛ- ወይዘሮ ፋንታዬ ወንድም —–የቦርድ አባል
4ኛ- አቶ ሽኩሪ መሀዲን———–የቦርዱ አባል
5ኛ- ዶክተር ብሩክ ላጲሶ ———-የቦርድ አባል
6ኛ- ወይዘሮ ሞሚና መሀመድ—— የቦርድ አባል
7ኛ – አቶ በሻላ ገመቹ ————- መርማሪ ቦርድ አባላት ሆነው ተሰይመዋል።
አባላቱ ሹመትም በምክር ቤቱ በ12 ተቃውሞ በ5 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
የመርማሪ ቦርድ አባላቱም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈፀማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።