አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)127ኛው የዓድዋ ድል በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በበዓሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳና የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱልሙኒየም አብዱልዋሂድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡
በበዓሉ ታሪክን የሚዘክሩ እና አንድነትን የሚያጠናክሩ የተለያዩ መልዕክቶች እየተላለፉ መሆናቸውንም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ-መስተዳድር ጽኅፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

