Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቪዬሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲነት አደገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ ወደ ዩኒቨርሲቲነት ማደጉ ተገለጸ፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ”ኤሮስፔስ” እና በመስተንግዶ መርሐ-ግብሮች የምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን መጀመሩም ከአቪየሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የበረራ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ በዕድሜ አንጋፋ እና ግዙፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በባለቤትነት የሚያስተዳድረው አቪዬሽን አካዳሚው ÷ የአብራሪነት፣ የአውሮፕላን ጥገና ፣ የካቢን ቡድን፣ የጉዞ ቲኬት ሽያጭ እና አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ሥልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷልም ነው የተባለው።
የአቪየሽን ትምህርት ቤቱ ወደ ዩኒቨርሲቲነት ካደገ በኋላ በዲግሪ መርሐ-ግብሮች ÷ በኤሮኖቲካል ምኅንድሥና ፣ በአውሮፕላን ጥገና ምኅንድሥና እንዲሁም በበረራ አስተዳደር በባችለር ሣይንስ የትምህርት መርሐ-ግብር ሲያሰለጥን ቆይቷል፡፡
በቱሪዝም እና መስተንግዶ አስተዳደር ዘርፎች ደግሞ በአርት ባችለር ዲግሪ የትምህርት መርሐ-ግብር ሲያሰለጥን ቆይቷል፡፡
በተጨማሪም በአቪየሽን አስተዳደር የማኔጅመንት ኦቭ ቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ዲግሪ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱም ነው የተመለከተው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version