አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመገበያያ ስፍራዎች ኮቪድ19ን ለመከላከል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደንብ መሠረት አካላዊ መራራቅን ማክበር እንደሚገባ አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገበያዎች ለብዙዎች የገቢ ምንጭ በመሆናችው የማኅበረሰቡን የኑሮ ደኅንነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ብለዋል።
ሸማቾችም ለኑሮ ሸመታዎቻቸው በገበያ ላይ ጥገኛ ናቸው ያሉ ሲሆን የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር እያንዳንዱ የራሱን ድርሻ እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

