አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል አጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በጋምቤላ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ የክልል ማዕከል አመራሮች፣ የጋምቤላ ከተማ አመራሮች ፣ የሶስቱ ብሔረሰብ ዞን እና የሁሉም ወረዳ አስተዳዳሪዎች እየተሳተፉ ነው።
ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ መሆናቸውን ከጋምቤላ ክልል መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡