አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20 ፣2015( ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በድርቅ ለተጎዱ የኮንሶ ዞን ወገኖች 50 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ ከመዲናዋ ባለሃብቶች የተሰበሰበ ሲሆን፥ የተለያዩ አልሚ ምግቦችን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
ድጋፉን ያስረከቡት የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፥ በድርቅ ለተጎድ የኮንሶ ዞን ዜጎች የተደረገው ድጋፍ አለኝታነታችንን ለማሳየት የተደረገ ነው ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው፥ከተማ አስተዳደሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይ የሚደረጉ ሰብዓዊ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
ባለፉት አራት ዓመታት በዝናብ እጦት ምክንያት ድርቅ ከተከሰተባቸው የሀገራችን አካባቢዎች የኮንሶ ዞን አንዱ ሲሆን፥ በድርቁ ምክንያት ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው ለመሄድ መገደዳቸው ተጠቁሟል።
በኮንሶ ዞን ብቻ ከ227 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ነው የተገለጸው።
በዓለምሰገድ አሳዬ
All reactions:
99

