Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ በጋሞ ዞን ያስገነባውን ካምፕ አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ በጋሞ ዞን በምዕራብ አባያ ወረዳ ያስገነባውን ካምፕ አስመረቀ፡፡

ካምፑ ለደቡብ ዕዝ  መከላከያ ሰራዊት የተሰራ ሲሆን የጦር መምሪያ፣ የሻላቃ መኮንኖች  መኖሪያና መስሪያ ካምኘ ያካተተ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በምረቃ ስነ  ስርዓቱ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ጀነራል መኮንኖች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመርሐ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷የሀገር ሠላም በአስተማማኝ ጠንካራ መሠረት ጸንቶ እንዲቀጥል ሠራዊቱ ሚናውን በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

የሀገር ሠላም በጠንካራ መሠረት ላይ ታንፆ እንዲቆም ሠራዊቱ ኃላፊነቱን በበለጠ ብቃት እንደሚወጣም ተናግረዋል፡፡

የተገኘውን ሠላም ለማጽናት ሠራዊቱ እየከፈለ ያለው መስዕዋትነት ሊደገፍ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

 

Exit mobile version