አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023 የአፍሪካ ሴቶች ሽልማት ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው ስነ ስርዓት በአመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ እና በየአካባቢያቸው በጎ ተፅዕኖ ያሳደሩ የአፍሪካ ሴቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከተሸላሚዎች መካከል ኢትዮጵያውያን ሴት ባለስልጣናት የሚገኙበት ሲሆን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋየ (ዶክተር) አንዷ ተሸላሚ መሆናቸውን ከሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡