አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በ2 ቢሊየን ብር ወጪ ዘመናዊ የቱሪስት ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተደድር ሙስጠፌ መሀመድና በመከላከያ ሚኒስትሩ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተመራ የፌዴራልና የክልል ልዑካን ቡድን በሶማሌ ክልል ዘመናዊ የቱሪስት ማዕከል ለመገንባት የታሰበ ምቹ ቦታን ለይቷል፡፡
የቱሪዝም ልማት ፕሮጀክቱ በክልሉ ሸበሌይ ወረዳ ዙሪያ በሚገኙት ተራሮች ሥር እንደሚገነባ የተገለፀ ሲሆን÷ ለፕሮጀክቱ እስከ 2 ቢሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግበትም ታውቋል፡፡
የቱሪስት ማዕከሉ ዘመናዊ ሆቴሎች፣ የባህል ማዕከላልና ዘመናዊ የቱሪስት ግድቦችን ያካተተ መሆኑን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡