አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ፣ ባሌና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ የተመዘገቡ ድልና ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
በሰልፉ ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት ለሀገራችን እድገት ዋስትና ነው፣ መጋቢት 24 የመንግስትን ስርዓት በሴራና ሃይል የመቀየር አስተሳሰብን የዘጋ ታሪካዊ ቀን ነው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጎንህ ነን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ተደምጠዋል፡፡
በድጋፍ ሰልፉ በርካታ ቁጥር ያላቸው በዞኖቹ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!