Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ላኪ አባል ሀገራት “ኦፔክ”ለዓለም አቀፉ ገበያ የሚያቀርቡትን የነዳጅ መጠን ለመቀነስ መወሰናቸውን አስታወቁ።

ሀገራቱ በቀን በ1 ነጥብ 16 ሚሊየን በርሜል ነው ለመቀነስ የተስማሙት።

ነዳጅ ላኪ አባል ሀገራቱ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ሥምምነታቸውን እንደሚተገብሩም ነው አልጀዚራ የዘገበው፡፡

አባል ሀገራቱ የዓለም አቀፉን ገበያ ለማረጋጋት በሚል የወሰዱት አስገራሚ እርምጃ ሠሞኑን በአሜሪካ መሥተዋል የጀመረውን የገበያ መረጋጋት ወደ ኋላ የመለሰ ነው ተብሏል፡፡

አሁን ላይ በአሜሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል ከ4 ነጥብ 17 ዶላር ወደ 79 ነጥብ 84 ዶላር ማሻቀቡም ተጠቁሟል፡፡

ሁኔታው “በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስተዋለው የዋጋ ግሽበት ይረጋጋል” የሚለውን ተሥፋ እንዳደበዘዘውም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version