Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮ – አንጎላን ግንኙነት ማጠናከር ይገባል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለበርካታ ዓመታት የዘለቀውን የኢትዮ-አንጎላ ወዳጅነት በቢዝነስ ዘርፉም ማጠናከር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

አቶ ደመቀ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የአንጎላ አምባሳደር ፉራንሲስክ ጆስ ዲክሩዝን አሰናብተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት እንዲጠናከር አምባሳደሩ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢትዮ- አንጎላ ግንኙነት ከተለመደው ፖለቲካ ባሻገር በቢዝነስና እና ኢቨስትመንት የማደግ እድል እንዳለው አቶ ደመቀ አስረድተዋል፡፡

አምባሳደር ፉራንሲስክ ጆስ ዲክሩዝ የኢትዮጵያ ባለሀብቶች በአንጎላ ለመሰማራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version