Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወደ ትግራይ ክልል የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ዳግም ለማስጀመር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ትግራይ ክልል የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ዳግም ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴዔታዎች አቶ በርኦ ሀሰን እና አቶ ደንጌ ቦሩ÷ በትግራይ ክልል ተገኝተው የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ዳግም ለማስጀመር ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር መክረዋል፡፡

የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዳግም የሚጀመርበትንና አጠቃላይ የትራንስፖርት ተቋማት እና መሠረተ ልማቶች ያሉበትን ሁኔታም ተመልክተዋል።

በቀጣይም በትራንስፖር እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ከትራንስፖርት ቢሮና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሥራዎች እንደሚሰሩ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

 

Exit mobile version