Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጀማ ወንዝ ላይ ጊዜያዊ መሸጋገሪያ ተሰርቶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀማ ወንዝ የብረት ድልድይ ወደ ነበረበት እስከሚመለስ ድረስ በተሰራው ጊዜያዊ መሸጋገሪያ ተሽከርካሪዎች መጓጓዝ ጀምረዋል፡፡

የጀማ ወንዝ የብረት ድልድይን ወደ ነበረበት ለመመለስ የ24 ሰዓት የጥገና ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሰረት ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች በጊዜያዊነት የሚተላለፉበት መሸጋገሪያ ተሰርቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የመንገዶች አስተዳደር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዋናውን የብረት ድልድይ ወደ ነበረበት ለመመለስ እየተደረገ ያለው ርብርብም እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጿል።

Exit mobile version