Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትንሳኤ እና የኢድ በዓላትን ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ገበያውን የሚረብሹ ደላሎችን ከገበያ ስርዓቱ በማስወጣት ቀጣይ ለሚከበሩ የትንሳኤ እና የኢድ በዓላት በቂ ዝግጅት መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የበዓላቱን አከባበር አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ አቶ ገ/መስቀል ጫላ ላለፉት 20 ቀናት ለበዓሉ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ምርቶችን ወደ መዲናዋ ለማስገባት ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በአላቱን መነሻ በማድረግ በመሠረታዊ ሽቀጦች ላይ የአቅርቦት ችግር እና ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚመራው የጋራ ግብረ ሃይልም የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ለበአላቱ የአቅርቦት ችግር እንዳይኖር አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ ምርቶች እየገቡ መሆኑ ተነስቷል፡፡

ለበዓላቱ በክልሎችና በከተሞች ለሸማቹ ምርቶችን በበቂ መጠንና በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና የግብርና ምርቶች እንስሳት፣ የእንስሳት ተዋጽኦ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ስንዴ ዱቄት ፣ ጥሬ በቆሎ፣ በስፋት ቀርቦ እየተሸጠ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ÷በክልሉ ስምንት ኀብረት ስራ ማኅበራት 127 ሺህ 700 ኩንታል ስንዴ እና 400 በሬዎችን እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል፡፡

በአማራ ክልል ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ዋና ዋና የግብርና ምርቶች እንስሳት፣የእንስሳት ተዋጽኦ፣ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ዱቄት ስንዴ፣ ጥሬ በቆሎ፣በስፋት ቀርቦ እየተሸጠ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በክልሉ ስምንት ኅብረት ስራ ማኅበራት 208 ነጥብ 176 ኩንታል ጤፍ ያቀርባሉ ነው የተባለው ፡፡

በተመሳሳይ ÷በደቡብ ከላይ በሌሎች ክልልሎች የተጠቀሱት የግብርና ምርቶች በአምስትኅብረት ስራ ማኅበራት እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች 93 ሺህ 890 ኩንታል ጤፍ፣ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን እንቁላል፣ 352 ኩንታል ቂቤ እና አይብ፣ 2 ሺህ 324 በሬዎች እንደሚቀርቡ ተነግሯል፡፡

በሌሎች ክልሎችም ለበዓላቱ የሚስፈልጉ የተጠቀሱት የግብርና ምርቶችና ሌሎች ግብዓቶች በኅብረት ስራ ማኅበራት በኩል በበቂ ሁኔታ እንደሚቀርብ ነው የተመላከተው፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version