Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ120 ሰዎች ክስ ተቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ማረሚያ ቤት የነበሩና በፍትሕ ሚኒስቴር አማካኝነት ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩ 120 ታራሚዎች ክስ ተቋርጦ ዛሬ ተለቀዋል።

በባለፉት ዓመታት ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩ ታራሚዎች ክስ ሲቋረጥ ይህ ለ3ኛ ጊዜ መሆኑን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ይቅርታና ምኅረት የተደረገላቸው ሰዎች ወደ ማሕበረሰቡ ተቀላቅለው መደበኛ ኑሯቸውን እንዲመሩ በመንግሥት በኩል ለተደረገላቸው ይቅርታ አመስግነዋል፡፡

የወንጀልን አስከፊነት ከማስተማር ባለፈ ለቀጣናው ሰላም የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡም አረጋግጠዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version