አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን ልዩ ኃይል በአዲስ የማደራጀቱ ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑ የሲዳማ ክልል አስታወቀ፡፡
የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ እንደተናገሩት÷ የየክልል ልዩ ሀይሎችን ዳግም የማደራጀት ስራ ላይ እንደ ሀገርም ሰፊ ውይይትና ዝግጅት ተደርጎበት ወደ ስራ የተገባበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህ በክልሉ ደረጃ ከልዩ ኃይል አባላቱና አመራሩ ጋር በመመካከር አስፈላጊነቱ ላይም ታምኖበት ወደ ስራ እንደተገባ ነው የገለጹት፡፡
በተቀመጠው ሀገራዊ አሰራር መሰረትም ለዜጎች ደህንነትና ሰላም ሲባል ጠንካራ ሀገራዊ የፀጥታ መዋቅርን መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ እንደታመነበትም አብራርተዋል፡፡
በዚህም በተጠና መልኩ ከአባሉና ከአመራሩ ጋር በተገባ ስምምነት መሰረት ዳግም የመደራጀቱ ሂደት በጥቂት ቀናት የማከናወን ስራ እንደሚጠናቀቅ አመላክተዋል፡፡
የሲዳማ ክልል ልዩ ኃይል ከዚህ በፊት የተሰጠውን ክልላዊና ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በተገቢውና በኃላፊነት ሲወጣ መቆየቱን የተናገሩት ሀላፊው በአዲሱ አደረጃጀት ደግሞ ይበልጥ ለሀገራዊ ተልዕኮ የመስራት አሰራር እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተመስገን ቡልቡሎ

