አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ላፉት አራት ዓመታት የተስተካከለ የዝናብ ሁኔታ ባለመኖሩ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ለችግር የተጋለጡ 2 ሚሊየን 8 ሺህ ወገኖች ድጋፍ ይሻሉ ተባለ፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ስሩር እንደገለጹት÷ ከማረቆ እስከ ደቡብ ኦሞ ባሉት የስምጥ ሸለቆ ወረዳዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡
በ2014/15 የምርት ዘመን በዝናብ መቆራረጥ፣ ፈጥኖ መውጣት እና በወቅቱ ባለመጀመር ምክንያት በኮንሶ፣ ቡርጅ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ደራሼ እና አሌ ድርቁ በስፋት ተከስቷል ብለዋል፡፡
ድርቁ ወደ ርሃብ እንዳይቀየር የክልሉ አደጋ ሥራ አመራር ምክር ቤት ቡድን አደራጅቶ በዝርዝር እንዲጠና ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡
በጥናቱ ውጤት መሠረትም ከ15 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቅበት የነበረው ከ342 ሺህ በላይ ሔክታር ከድርቁ ጋር በተያያዘ ችግር መውደሙ ተረጋግጧል ነው ያሉት፡፡
ከዚህ ምርት ማግኘት የነበረባቸውን ወገኖች ጨምሮ በአጠቃላይ በደቡብ ክልል 2 ሚሊየን 8 ሺህ ዜጎች ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አቶ ኡስማን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ለዚህም መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም መላው ኢትዮጵያውያን ለድርቁ ተጋላጭ ወገኖች እና እንስሳት የሚውል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

