አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከጀርመን ልማት ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ያቀረባቸውን 17 የእርሻ ትራክተሮች ለሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ አስረከበ።
የልማት ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸዉ ዋጬ ÷ “አርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና ሜካናይዜሽን እርሻ ሥራ ተግባራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዲችል ዘመናዊ የእርሻ ትራክተር የማይናቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተዉጣጡት እና ትራክተሮቹን የተረከቡት አርሶ አደሮች በበኩላቸው ግንባር ቀደም በመሆን ወደ ግብርና ሜካናይዜሽን ዘርፍ መቀላቀላቸው በዘርፉ እየተካሄደ ያለውን ጥረት ወደ አንድ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ብለዋል፡፡
ትራክተሮቹን ለማስተላለፍ አርሶ አደሮቹ 20 በመቶ ቅድመ ክፍያ የፈጸሙ ሲሆን ቀሪ 80 በመቶውን ደግሞ በአምሥት ዓመታት ውስጥ መክፈል እንዲችሉ ብድር ተመቻችቶላቸዋል፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

