አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በህመምና በፈቃድ ምክንያት ወደ ሪፎርሙ ያልተቀላቀሉ ልዩ ኃይሎች እስከ መጪው ሰኞ ድረስ ወደሚፈልጉት የፀጥታ መዋቅር እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀረበ፡፡
በጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይሉን መልሶ የማደራጀቱ ሂደት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰናይ አክዎር ተናግረዋል፡፡
ክልሉ እንደ ሀገር ጠንካራ የፀጥታ ተቋም ለመገንባት የሚሰራውን ሪፎርም በመቀበል የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።
በዚህም በሀገራችንና በክልላችን ዘላቂ በሆነ መንገድ የሕዝባችንን አንድነት ለማስጠበቅ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
እንደ ሀገር ጠንካራ የፀጥታ ተቋም ለመገንባት መንግስት ያቀረበውን የልዩ ሀይል ሪፎርም በመቀበል ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ልዩ ኃይሉ ላደረገው ትብብርም ኮሚሽነሩ ምስጋና አቅርበዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

