Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሩሲያ እና ቻይና በወታደራዊ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር  ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይናው መከላከያ ሚኒስትር ሊ ሻንግፉ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ፑቲን በሀገራቱ ወታደራዊ ክፍሎች በኩል ጠቃሚ መረጃዎችን በመደበኛነት እንደሚለዋወጡ እና በወታደራዊ ቴክኒካል ትብብር ዘርፍ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ሀገራቱ ቀደም ሲል በሩቅ ምስራቅ እንዲሁም በአውሮፓ የምድር፣ የባህር እና የአየር ሃይሎችን ያሳተፈ ወታደራዊ ልምምድ ማካሄዳቸውንም አስታውሰዋል፡፡

የቻይና መከላከያ ሚኒስትር ሊ ሻንግፉ በበኩላቸው÷ ከቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ከነበረው በላይ  የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት  ይበልጥ መጠናከሩን ገልጸዋል፡፡

ቻይና በሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ክፍሎች መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ከአጋሯ ሩሲያ ጋር ለመስራት ፈቃደኛ መሆኗን አብራርተዋል፡፡

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ግጭት ውስጥ ከገባችበት ጊዜ ጀምሮ ቤጂንግ እና ሞስኮ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ወታደራዊ ዘርፎች ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version