አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት በ90 ቀናት የተገነቡ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡
በቀን ከ300 ሺህ እስከ 400 ሺህ ዳቦና ኬክ የማምረት አቅም ያለው በረከት የዳቦና ኬክ ማምረቻ ፋብሪካ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ በክፍለ ከተማው ቄራ አደባባይ የተገነባው የቂርቆስ ፓርክ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
በምረቃ ሥነ ስርዓቱ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ቡዜና አልቀድር እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ከድር (ዶ/ር ) ተገኝተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ እነዚህን ለነዋሪው የሚጠቅሙ ሥራዎች በጥራት እና በፍጥነት እንዲሠሩ በማድረግ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለሀብቶች እና ያስተባበሩ አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በፍቅርተ ከበደ

