Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሱዳን ኃይሎች የተኩስ አቁም ሥምምነቱን በመጣስ ውጊያ መቀጠላቸው ተሰምቷል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለ24 ሰዓታት የተኩስ አቁም ሥምምነት ቢደርሱም ውጊያው መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጣልቃ ገብቶ ካሸማገለና በሱዳን የተኩስ አቁም ሥምምነት ከተደረሰ ከሠዓታት ቆይታ በኋላም ጦርነቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡

መሬት ወርዶ መታየት የነበረበት ሥምምነት ያልተተገበረው የሀገሪቷ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ቁልፍ ቦታዎችን ለመያዝ ሽሚያ ውስጥ በመግባታቸው መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

የተኩስ አቁም ሥምምነቱን መጣስ በተመለከተም አንዱ ወገን ሌላኛውን ሲወነጅል ተስተውሏል ነው የተባለው።

በካርቱም በሚገኙ የቴሌቪዥን ማሠራጫ ጣቢያዎች የቀጥታ ሥርጭት መርሐ-ግብሮች ላይ ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ከጀርባ ሲሰማ እንደነበር ተጠቁሟል።

በሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በሚመሩት የሱዳን ጦር እና ምክትላቸው መሃመድ ሀምዳን ደጋሎ በሚመሩት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከል የተፈጠረው ግጭት አምሥተኛ ቀኑን አስቆጥሯል፡፡

በግጭቱም እስካሁን 200 በላይ ንጹሃን ዜጎች ለኅልፈት መዳረጋቸውን ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version