Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

13ኛው የአፍሪካ የቆዳ ምርቶች የንግድ አውድ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 13ኛው የመላው አፍሪካ የቆዳ ምርቶች የንግድ አውድ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።

አውድ ርዕዩ የተለያዩ ሀገራት የቆዳ ውጤት አምራቾች፣ የማሽነሪዎችና ግብዓት አቅራቢዎች፣ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ተቋማት እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት በተገኙበት ነው የተከፈተው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል አውደ ርዕዩን  መርቀው ሲከፍቱ እንደተናገሩት÷ኢትዮጵያ ለአምራች ዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው፡፡

13ኛው የመላው አፍረካ የቆዳ ውጤቶች አውደ ርዕይም ኢትዮጵያ ለያዘችው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ግንባታ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ሬድማን በዳዳ በበኩላቸው ÷ ዓውደ ርዕዩ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር የሚያገናኝ  መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በተለይም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተቀዛቅዞ የቆየውን የቆዳ ኢንደስትሪ ዘርፍ ማነቃቃት እንደሚያስችል ነው የተናገሩት፡፡

የንግድ ትርዒቱን ከ15 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እና ከ2 ሺህ በላይ የውጪ ሀገራት ዜጎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

Exit mobile version