አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዕጣ የወጣባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ማጠናቀቂያ ሥራዎች ለመጨረስ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ::
የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ ÷ የ20/80 እና 40/60 ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የማጠናቀቅ ሥራ በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ነው ብለዋል።
ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹን ለማጠናቀቅ የከተማ አሥተዳደሩ ከራሱ በጀት ወጪ በማድረግ እየሠራ እንደሆነም ነው የተናገሩት።
ዕጣ የወጣላቸው ነዋሪዎች ቤታቸውን እንዲረከቡ ግንባታ የማጠናቀቅ ሥራዎችን በሌሊትም ጭምር እየተሠሩ መሆናቸውን የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ ነባር ዕጣ የወጣላቸው ነዋሪዎች እስከ ሠኔ 30 ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፣ የቀበሌ ቤት ይዘው የሚገኙ ዕጣ የወጣላቸው አንዳንድ ነዎሪዎችም ከሰኔ 30 በኋላ የመልቀቅ ግዴታ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡
በአዲሱ ሙሉነህ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

