Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሶዶ ኦሮሞ ሜልባ ገዳ ምሥረታ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሶዶ ኦሮሞ ሜልባ ገዳ ምሥረታ በሰዴን ሶዶ ወረዳ ኦዳ ከለቻ ተካሄደ።

ባለፉት ሥርዓቶች የሶዶ ኦሮሞ በደረሰበት የተለያዩ ጫናዎች ምክንያቶች የገዳ ሥርዓቱን አቋርጦ መቆየቱ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተነግሯል።

ተቋርጦ የነበረው የሶዶ ኦሮሞ ገዳ ሥርዓት የቱለማ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ጸሐፊ አባገዳ ጎበና ሆላ በተገኙበት በድጋሚ ተጀምሯል፡፡

ወሰኑ ጎንፋ የሶዶ ኦሮሞ ሜልባ አባገዳ ሆነው በሶዶ ኦሮሞ አባ ሙዳ መሾማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ አባ ጨፌ፣ አባ ሰአ፣ አባ ሴራ እና አባ ማቲን ጨምሮ የገዳ ሰገሊ አባላትም ተሹመዋል።

የሶዶ ኦሮሞ ሜልባ ገዳ ሥርዓት ምሥረታው የገዳ ሥርዓት እሴቶችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ይረዳል ተብሏል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተወጣጡ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version