Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአቶ ርስቱ ይርዳ የተመራ ልዑክ በሥራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ የተመራ ልዑክ በወላይታ ዞን በሥራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን ጎበኘ፡፡

ልዑኩ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችንና የምክር ቤት አባላትን ያካተተ ነው፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት በወላይታ ዞን በዳሞት ሶሬ ወረዳ በሰብል ልማት ተደራጅተው ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን መጎብኘቱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም የልዑካን ቡድ አባላት በሶዶ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞችን እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል፡፡

Exit mobile version