Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢፌዴሪ አየር ሀይልን የለውጥ ጎዳና የሚዳስስ ዘጋቢ ፊልም ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰማዩ የኛ ነው” በሚል የኢፌዴሪ አየር ሀይል የመጣበትን የለውጥ ጎዳና እና አሁን ያለበትን ቅርጽ የሚዳስስ ዘጋቢ ፊልም ተመርቋል።

ኩራት ፒክቸርስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በመተባበር የሰራው ዘጋቢ ፊልሙ የአንድ ሰዓት ተኩል ፍጆታ አለው።

ዘጋቢ ፊልሙ የኢፌዴሪ አየር ሀይልን የለውጥ ስራዎች እና ገድል ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመ ነው ተብሏል።

የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ÷አየር ሀይሉ ባለፉት አመታት ኢትዮጵያን በሚመጥን ልክ እየተገነባ ነው ብለዋል።

የኢፌዴሪ አየር ሀይል ግንባታው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ እንዲተርፍ ሆኖ ነው እየተሰራ ያለውም ብለዋል ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡

የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሌተናል ኮለኔል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው ÷የአየር ሀይሉን ራዕይ የሚያሳይ ሆኖ የተሰራው ዘጋቢ ፊልሙ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ተቋሙን እንዲቀላቀሉ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

አየር ሀይሉ ባለፉት አመታት በሰው ሀይል ግንባታ፣ ትጥቅ በማዘመን፣ በውጊያ መሰረት ልማት ግንባታ እና ምቹ የስራ ከባቢ በመፍጠር ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱንም ገልጸዋል ።

በአላዛር ታደለ

Exit mobile version