አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል እንደደረሰበት ገለጸ፡፡
በሀገር ውስጥ በቂ የነዳጅ አቅርቦት መኖሩ እየታወቀ የነዳጅ ዕጥረት ይከሰታል የሚሉ አዋኪ መልዕክቶች ሆነ ተብለው የሚነዙ መሆኑን ሕብረተሰቡ እንዲገነዘብ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
በቀጣይም በነዳጅ ማደያዎች ላይ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየት እና ዕጥረት መፍጠርን የመሳሰሉ ችግሮች በሚፈጥሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ያስጠነቀቀው፡፡
በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ምክንያት ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም የሚያስችል አካውንት ካለመክፈት ጋር የተያያዘ እንጅ የነዳጅ ዕጥረት አለመሆኑንም ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

