Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሱዳን ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኝበት አካባቢ የውጊያ ቀጠና መሆኑ፣ በአካባቢው የመብራት አገልግሎት መቋረጡና የምግብ ቁሳቁስ ለማግኘትም ሆነ ከኤምባሲ ወጥቶ መግባት እንደማይቻል ተጠቁሟል፡፡
 
በዚህ ሁኔታ ዜጋን መርዳት ስለሚያዳግትና የዲፕሎማቶች ህልውናም አደጋ ላይ ስለሚወደቅ በኤምባሲው የተወሰኑ ሰራተኞች እዲቀሩ ተደርጎ አምባሳደሩን ጨምሮ ቀሪዎቹ ደግሞ ከገዳሪፍ ስራቸውን እያከናውኑ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
 
ለዜጎች ሊደረግ የሚችለው ድጋፍም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version