Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፋር ክልል መንግስት በአቶ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡

ክልሉ በሃዘን መግለጫው÷ የሠላም ምህዳሩ ሰፍቶ ነገሮች ሁሉ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሄ እያገኙ ባለበት በዚህ የብርሃን ወቅት፣ ወደ ኋላ በመመለስ ጨለማን በመምረጥ በውይይትና በንግግር፣ ሃሳብን በሀሳብ ማሸነፍ እየተቻለ እንደዚህ ያለ እኩይ ተግባርን መፈፀም የተሸናፊዎች ስነ-ልቦና መገለጫ ነው ብሏል።

አቶ ግርማ የሺጥላ ባለ ብሩህ አእምሮ እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ሀሳቦችን የሚያመነጭ፣ በተግባርም የሚገልፅ፣ ወደፊትም በርካታ አበርክቶዎችን ለሀገሩ ያበረክታል ተብሎ የሚጠበቅ ውድ የሀገር ልጅ እንደነበርም አንስቷል፡፡

የክልሉ መንግስት እኩይ አላማን ባነገቡ አካላት ህይወቱ ሊቀጠፍ በመቻሉ የተሰማውን ልባዊ ሃዘን ገልጿል፡፡

ለአቶ ግርማ የሺጥላ ቤተሰቦች፣ ባልደረቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የአማራ ክልል ህዝብም መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

 

Exit mobile version