Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የታክስ አስተዳደር ለማዘመን እደግፋለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ባንክ የኢትዮጵያን የታክስ አስተዳደር ለማዘመን አስፈላጊውን ቴክኒካዊ እና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ቱሉ በታክስ አስተዳደር ሥርዓት፣ ቴክኖሎጂና የሰው ኃብት አስተዳደር ተግባራት ላይ ከዓለም ባንክ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

የግብር አከፋፈል ሥርዓቱን ለማዘመን በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የዓለም ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ አቶ ተስፋዬ ጠይቀዋል፡፡

የዓለም ባንክ ተወካይ ማኑኤል ቫርጋስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በገቢው ዘርፍ እያሳየች ያለው ለውጥ እጅግ አበረታች እና ተስፋ ሰጪ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓለም ባንክ የታክስ አስተዳደሩን ለማዘመን አስፈላጊውን ቴክኒካዊ እና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

የቴክኖሎጂ፣ የሰው ኃብት እና ሌሎች ሥራዎች ከግብ እንዲደርሱ ባንኩ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር አብሮ እንደሚሠም ነው ያረጋገጡት፡፡

ድጋፉ በሚደረግባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንደሚተገበር አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version