Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሥራ መዳረሻ ሀገራትን ለማስፋት የሚደረገው ጥረት መቀጠሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ መዳረሻ ሀገራትን ለማስፋት የሚደርገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ፡፡

የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ስዊድን መላክ ስለሚቻልበት ሁኔታ በስዊድን እና አካባቢው ሀገራት የሥራ አመቻች አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም ስዊድን የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ያላት መሆኑን በሀገሪቱ ከፍተኛ እውቅና ካለው ኩባንያ መረዳት ተችሏል ተብሏል፡፡

በቀጣይም ይህ አማራጭ ለዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ በጋራ ለመሥራት ከስምምነት መደረሱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version