Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለፉት 9 ወራት ተኪ ምርት በማምረት ከ 129 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 9 ወራት ተኪ ምርት በማምረት ከ 129 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡

ኮርፖሬሽኑ የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በጅማ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

በግምገማ መድኩ ላይ በቀረበው ሪፖርት እንደተገለጸው ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሀገር ውስጥ ገበያ የተለያዩ ምርቶችን በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ጫናን ከመቀነስ አኳያ አበረታች ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

በዚህም ከ125 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ለማዳን ታቅዶ ከ 129 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማዳን ተእሏል መባሉን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኮርፖሬሽኑን አገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም በማድረግ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር የበለጠ በመቀራረብ የተሠራው ከፍተኛ የንቅናቄ ስራ ለውጠየቱ መመዝገብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በ2015 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ ከ121 ሚሊየን 934 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ማግኘቱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በግምገማው ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከርና ባጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ በቀጣይ 3 ወራት በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ይጠበቃል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version